306480494_639826217503400_4582540479198187617_n

“ቡናችን ለአብሮነታችን እና ብልጽግናችን” በሚል መሪ ሃሳብ ባዘጋጀው የእውቅናና የሽልማት መርሃ ግብር

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን “ቡናችን ለአብሮነታችን እና ብልጽግናችን” በሚል መሪ ሃሳብ ባዘጋጀው የእውቅናና የሽልማት መርሃ ግብር ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የላቀ ድርሻ ለነበራቸው አካላት በተለይም ለአርሶ አደሮች ሸልማቶችን መስከረም 5 ቀን አበርክተዋል። ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በቡና 1.4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አስገኝታለች። ፕሬዚደንቷ በንግግራቸው “የግሉ ዘርፍ እንዲሳተፍ የላቀ ሚና እንዲጫወት ለአገራችን በር የሚከፍት ነው … ያለ ግሉ ዘርፍ የአገር እድገት የለም” ሲሉ ገልፀዋል። አክለውም “ቡና የኤክስፖርትን ምርት ከማሳደግ ያለፈ እሴት አለው፤ ሰዎችንና ማህበረሶችን የሚያገናኝ፣ የመወያያ፣ ሃሳብ የመለዋወጫ መድረክ፣ ጎረቤት ለጎረቤት የሚያገናኝ ነው” ብለዋል። ባለፈው ዓመት ኢትዮጵያ ካስገኘችው የውጭ ምንዛሬ 72% የሚሸፍነው የግብርና ምርቶች ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ 35% የሚሆነው በቡና የተያዘ ነው። በዚህ ለተሳተፉ የቡና ገበያ ባለድርሻ አካላትን ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ አመስግነዋል። ለሥራቸውና ለልፋታቸው እወቅና መስጠት ለወደፊቱ ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ገልፀዋል።

The Ethiopian Coffee and Tea Authority organized on September 15 a recognition and reward program under the theme “our coffee for our unity and prosperity” where President Sahle-Work Zewde gave awards to those who made outstanding contributions especially farmers. Ethiopia earned, for the first time, 1.4 billion dollars in coffee. In her speech, the President explained that “it has opened the door for the private sector to play a paramount role … a country’s development depends also on the private sector”. She added that “coffee’s value is beyond increasing export production; it connects people and communities, it’s a place for discussion, for exchanging ideas, it connects neighbors”. Last year, agricultural products accounted for 72% of Ethiopia’s foreign exchange earnings of which 35% was coffee. President Sahle-Work acknowledged the coffee market stakeholders for their contribution. She said that recognizing their work and effort will generate great potential in the future.

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *