308632400_456239109871839_6495369836903445685_n

የደም ልገሳ መርሐ ግብር ተካሄደ !!

የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን አመራር እና ሰራተኞች በዛሬው እለት ለወገኖቻችን አጋርነታቸውን ለማሳየት የደም ልገሳ መርሐ ግብር አካሂደዋል !!

በባለስልጣን መ/ቤቱ በተካሄደው በዚህ የደም ልገሳ ፕሮግራም ላይ ከፍተኛ አመራሩ እና ከተለያዩ ክፍሎች የተውጣጡ ከ20 በላይ ሰራተኞች በሙሉ ፈቃደኝነት ላይ ተመስርተው የደም ልገሳውን ማከናወናቸው አገራችን በአሁኑ ሰአት ካለችበት ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ተገቢ መሆኑን እና ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ክቡር ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር አዱኛ ደበላ ተናግረዋል ። በደም ልገሳው ላይ የተሳተፉትንም አመስግነዋል ።

አቶ መሀመድ ሸምሱ በባለስልጣን መ/ቤቱ የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ሀላፊ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የተደቀኑባትን በርካታ ችግሮች ከህዝቡ እና መንግስት ጋር በመቀናጀት እየተወጣች መሆኑን እና የዚህ የዛሬው ደም ልገሳም አንዱ አካል እንደሆነና ከስጦታዎች ሁሉ የላቀ እንደሆነ አስረድተዋል ።

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *