የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን “ቡናችን ለአብሮነታችን እና ብልጽግናችን” በሚል መሪ ሃሳብ ባዘጋጀው የእውቅናና የሽልማት መርሃ ግብር ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የላቀ ድርሻ ለነበራቸው አካላት በተለይም ለአርሶ አደሮች ሸልማቶችን መስከረም 5 ቀን አበርክተዋል። ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በቡና 1.4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አስገኝታለች። ፕሬዚደንቷ በንግግራቸው “የግሉ ዘርፍ እንዲሳተፍ የላቀ ሚ ...