በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ ቡና ማዘጋጃና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች ተጎበኙ፡፡

በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ ቡና ማዘጋጃና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች ተጎበኙ፡፡
June 22, 2020 No Comments News admin

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ያዘጋጀው እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የተገኙበት የመስክ ጉብኝት ተካሂዷል፡፡ ጉብኝቱ የተካሄደው በአዲስ አበባ እና በዙሪያው በሚገኙ የተለያዩ ቡና ማዘጋጃና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች ሲሆን ክብርት ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ የግብርና ሚኒስቴር ሚ/ር ዴኤታ እና ክቡር ዶ/ር አዱኛ ደበላ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ተገኝተውበታል፡፡
ዶ/ር አዱኛ እንደተናገሩት በአገራችን ከሚገኙ የግብርና ምርቶች ውስጥ በኤክስፖርት ግኝቱ በመጀመሪያ ደረጃ ላይ የሚገኘው ቡና ለአገሪቱ ኢኮኖሚ ያለው አስተዋፅዖ ከፍተኛ ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶት በመሰራት ላይ የሚገኝ ሲሆን በተካሄዱ የሪፎርም ስራዎች እና ከላኪዎች ጋር በተደረጉ የጋራ ጥረቶች ከታቀደው በላይ ገቢ ተገኝቷል፡፡
በመሆኑም ይህን ውጤት አጠናክሮ ለመቀጠል በተለይም ከላኪዎች ጋር በቅርብ በመገናኘት ባሉ ችግሮች እና መልካም አጋጣሚዎች ዙሪያ መነጋገር ያስፈልጋል፡፡ ይህን መሰሉ ተግባር ከባለፈው ዓመት ጀምሮ በስፋት እየተሰራበት መሆኑን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ፤ በዚህም አበረታች ለውጦች ተገኝተውበታል፡፡ ዘንድሮም ላኪዎች የቡና ምርት በስፋት እንዲያወጡና ለዓለም ገበያ እንዲያቀርቡ የማነቃቃት ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ክብርት ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ በበኩላቸው ዘርፉን ለመደገፍ የመንግስት ቁርጠኝነት መኖሩን ገልጸው በተመለከቱት ነገር ግን መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡

Total Page Visits: 799 - Today Page Visits: 3
About The Author

Leave a reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *