የኢትዮጵያ ቡናዎች ሽያጭ በዓለም አቀፍ ገበያ ለጨረታ ቀርበው ከፍተኛ ዋጋ አውጥተው በትናንትናው እለት ተሸጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቡናዎች ሽያጭ በዓለም አቀፍ ገበያ ለጨረታ ቀርበው ከፍተኛ ዋጋ አውጥተው በትናንትናው እለት ተሸጠዋል፡፡
June 29, 2020 No Comments News admin

በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የባለ ልዩ ጣዕም ቡና ቅምሻ (Cup of Excellence – Ethiopia) ውድድር አሸናፊ የሆኑት የኢትዮጵያ ቡናዎች ሽያጭ በዓለም አቀፍ ገበያ ለጨረታ ቀርበው ከፍተኛ ዋጋ አውጥተው በትናንትናው እለት ተሸጠዋል፡፡ በውድድሩ አንደኛ የወጣው የአርሶ አደሩ የአቶ ንጉሤ ገመዳ ሙዴ ቡና አንዱ ፓውንድ በ185.10 የአሜሪካ ዶላር ተሸጧል፡፡ ይህም አንዱ ኪሎ ቡና ብር 14,452.00 ብር እንዳወጣ ያመለክታል፡፡ ከሁለተኛ ደረጃ ጀምሮ የወጡ ቡናዎችም ከፍተኛ ዋጋ አግኝተዋል፡፡ በውድድሩ የተሳተፋችሁትና ለውጤት የበቃችሁት የቡና ገበሬዎች እንኳን ደስያላችሁ፡፡ ይህ ስኬት ኢትዮጵያ ያላትን የባለ ልዩ ጣዕም ቡና ለዓለም ገበያ ይበልጥ ያስተዋወቀ፣ የገበያ አድማሳችን እንዲሰፋ በር የሚከፍትና በጥራት የሚመረት ቡና በገበያ ላይ ያለውን ተፈላጊነት ያመላከተ ነው፡፡ ይህ ውድድር በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲካሄድ ያስተባበሩትን አካላት በሙሉ እናመሰግናለን፡፡

Total Page Visits: 1579 - Today Page Visits: 2
About The Author

Leave a reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *