በ2012 በጀት ዓመት በቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ኤክስፖርት የተሻለ አፈጻጸም ለነበራቸው እውቅና ተሰጠ፡፡

በ2012 በጀት ዓመት በቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ኤክስፖርት የተሻለ አፈጻጸም ለነበራቸው እውቅና ተሰጠ፡፡
August 19, 2020 No Comments News admin

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በ2012 በጀት ዓመት በቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ኤክስፖርት የተሻለ አፈጻጸም ለነበራቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች እውቅና ሰጥቷል፡፡ 
በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል በተካሄደው የእውቅና አሰጣጥ እና ሽልማት ስነ ስርዓት ላይ ክቡር አቶ ዑመር ሁሴን የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ተገኝተው እንደተናገሩት “ከ1997 ጀምሮ ወደ ታች ሲወርድ የነበረው የኤክስፖርት ግኝት ለመጀመሪያ ጊዜ በጥሩ ሁኔታ የተሻለ አፈጻጸም አሳይቷል፡፡ ለዚህ ደግሞ ከፍተኛውና 80 በመቶው ቡና ሲሆን ለዚህ ደግሞ ባለስልጣን መ/ቤቱ በየደረጃው ካሉ አካላት ጋር በጥምረት በመስራት ያመጣው ውጤት በመሆኑ ለስራችሁ ልትመሰገኑ ይገባችኋል፡፡” ብለዋል፡፡
ክቡር ዶ/ር አዱኛ ደበላ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው ኢትዮጵያ 270 ሺህ ቶን ቡና ለመጀመሪያ ጊዜ ለዓለም ገበያ ማቅረቧን ተናግረው ይህን ውጤት ለማምጣት ደግሞ በርካታ ጥረቶች መደረጋቸውን፤ በተለይ በግብይቱ በኩል የተካሄዱ የተለያዩ ማሻሻዎች እና የተደረጉ የፕሮሞሽን ተግባራት ለዚህ ተጠቃሽ እንደሆኑ አስታውሰው በዋናነት የባለስልጣን መ/ቤቱ ከአርሶ አደሩ፣ ከላኪዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተቀናጅቶ መስራቱ ለዚህ ውጤት እንዳበቃው ተናግረዋል፡፡ 
በእለቱ ክቡር አቶ ሻፊ ዑመር የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር የባለስልጣን መ/ቤቱን 2012 በጀት አመት ኤክስፖርት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን አቶ ግዛት ወርቁ የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅም አጠቃላይ በማህበሩ በኩል የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት አቅርበው ውይይት ከተካሄደ በኋላ በበጀት ዓመቱ በቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ኤክስፖርት የተሻለ አፈጻጸም ለነበራቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል፡፡

Total Page Visits: 1395 - Today Page Visits: 3
About The Author

Leave a reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *