ኦን ላይን የኤሌክትሮኒክስ የግብይት አሠራር ዙሪያ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው

ኦን ላይን የኤሌክትሮኒክስ የግብይት አሠራር ዙሪያ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው
October 28, 2020 No Comments News admin

ኦን ላይን የኤሌክትሮኒክስ የግብይት አሠራር ዙሪያ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው!!የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር ያዘጋጀውና ኦን ላይ የኤሌክትሮኒክስ የግብይት አሠራርን የተመለከተ ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡

ስልጠናው እየተካሄደ ያለው በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሰልጣን መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን ክቡር አቶ ሻፊ ዑመር የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የገበያ ልማትና ቁጥጥር ዘርፍ ምክ/ዳይሬክተር ከፍተውታል፡፡ አቶ ግዛት ወርቁ የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅም ተገኝተዋል፡፡አቶ ኸይሩ ኑሩ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የገበያ መረጃና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እንዳሉት ስልጠናው የተዘጋጀው ከሀምሌ 1 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ የዋለውን የኤሌክትሮኒክስ የአንድ መስኮት አገልግሎት ኤሌክትሮኒክስ ሲስተም አሞላልን በተመለከተ ነው፡፡ ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ ሲገባበትም ስራዎችን ቀልጣፋና ዘመናዊ እንደሚያደርግም ነው የተገለጸው፡፡

Total Page Visits: 1704 - Today Page Visits: 3
About The Author

Leave a reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *