የፀረ ሙስና ቀን በፓናል ውይይት ተከብሮ ዋለ!!

የፀረ ሙስና ቀን በፓናል ውይይት ተከብሮ ዋለ!!
December 9, 2020 No Comments News admin

በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ዛሬ ህዳር 30/2013 ዓ.ም በባለስልጣን መ/ቤቱ አዳራሽ የፀረ ሙስና ቀን በፓናል ውይይት ተከብሮ ውሏል፡፡«ትውልድ የስነ ምግባር ግንባታን በጠንካራ ዲስፕሊን በመምራት ሌብነትንና ብልሹ አሰራርን በመታገል የብልጽግና ጉዟችንን እናፋጥናለን»

በሚል ቃል የተከበረውን የፀረ ሙስና ቀን ዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊን በመወከል በንግግር የከፈቱት አቶ ሀብቱ ተክሉ የግዢና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሲሆኑ ዓለማቀፍ የጸረ ሙስና ቀን ባለፉት ዓመታት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ16 ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ መከበሩን አስታውሰው ሙስናን እና ብልሹ አሰራር የሚጸየፍ ትውልድ ከመቅረጽ አንጻር የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን እና ሰራተኛውም በተሰማራበት መስክ ሁሉ አስፈላጊውን ስነ ምግባርና ዲስፕሊን ተከትሎ ስራውን በታማኝነት መፈጸም እንዳለበት አሳስበዋል፡፡በፓናል ውይይቱ ላይ ዓለማቀፍ የጸረ ሙስና ቀንን አስመልክቶ የተዘጋጀ መነሻ ፅሁፍ አቶ ስንታየሁ ግርማ በባለስልጣን መ/ቤቱ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቅርበዋል፡፤ ዳይሬክተሩ አጠቃላይ በሙስና ምነነት፣ የሙስና አይነቶች፣ መገለጫቸው እና የሚያስከትሉትን ጉዳት በተመለከተ የተለያዩ አገሮችን እና የኢትዮጵያን ተሞክሮ በማጣቀስ አብራርተዋል፡፡ አቶ ፍሰሀ ከበደ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ በበኩላቸው በስነ ምግባር ክፍሉ እና በፌዴራል ስነ ምግባር ፀረ ሙስና ኮሚሽን ስትራቴጂዎች እና የ2013 ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ማብራሪያቸውን አቅርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በቦታው ተገኝቶ ዘግቦታል፡፡

Total Page Visits: 1463 - Today Page Visits: 3
About The Author

Leave a reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *