እኛ ችላ ብንለውም፣ እሱ ችላ አላለንም!

እኛ ችላ ብንለውም፣ እሱ ችላ አላለንም!
April 14, 2021 No Comments News admin

እኛ ችላ ብንለውም፣ እሱ ችላ አላለንም!ችላ ለማለት ደግሞ ጊዜው አሁን አይደለም! ኮሮና የስርጭት አድማሱን በከፍተኛ ሁኔታ እያሰፋ ነው፤የዛሬ አንድ አመት ሺ ሰዎች ተመርምረው 1,2,3 ወይም 4 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኘ ሲባል መንገዱ ጭርታ ነግሶበት፣ ውሀና ሳሙና ከሳኒታይዘር ጋር ለመንገደኛ ቀርቦበት፣ በየቢሮና አካባቢው እጅግ የሚደነቅ ጥንቃቄ የተደረገበት ወቅት ነበር፤ አሁንስ ለምን?ቫይረሱ የሰው ዘርን በሙሉ እያስጨነቀ በሽምጥ ግልቢያው መላውን ዓለምን እያዳረሰ ይገኛል። ውቅያኖስ፣ አህጉር፣ ድንበር፣ ከተማ፣ አካባቢ፣ ቀበሌ፣ ሰፈር፣ ጎረቤት እያለ አድማሱን ያጠበበው ኮሮና ሰሞኑን የየእያንዳንዳችንን ቤት በማንኳኳት ላይ ይገኛል፡፡ መልአከ ሞቶች እንደዋዛ በቅርብ ርቀት እየተመለከቱን፣ አድፍጠው መዘናጋታችንን እየጠበቁ ነው፡፡ ነገ ምን እንደሚፈጠር ባናውቅም እስካሁን ባለው መረጃ እየተመረመሩ ካሉ 4 ሰዎች መካከል 1 ሰው የኮሮና ቫይረስ እየተገኘባቸው ነው፡፡ ህይወት አንዲት ናት፣ ምትክ የላትም፡፡ ስለሆነም የሚቻለንን ያህል፣ የጥንቃቄ ጥግ ደርሰን ራሳችንን፣ የምንወዳቸውን እናት፣ አባት፣ ልጅ፣ ሚስት፣ ባል፣ ወንድም፣ እህት፣ ወዘተ. እናትርፍ፡፡ ‹‹ጥንቃቄ ይጠብቃል ማስተዋልም ይጋርዳል››፡፡ በመሆኑም እያንዳንዶቹን የመከላከያ መንገዶች የሆኑትን፤• ማስክ ሳናደርግ ባለመንቀሳቀስ፣• እጅ ባለመጨባበጥ፣ ባለመሳሳምና ባለመተቃቀፍ፣• እጅን በሳሙናና በውሃ በየጊዜው በደንብ በመታጠብ፤ ይህም ከቤት ከመውጣትዎ በፊት፣ ወደሚሄዱበት ቦታ እንደደረሱ፣ መጸዳጃ ቤት ከተጠቀሙ በኋላ ፣ ምግብ ከመመገብዎ በፊትና ከተመገቡ በኋላ፣ ከእረፍት መልስ እና ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በኋላ፣ ከማናቸውም ዓይነት ጨዋታ በኋላ፣ ከሄዱበት ቦታ ወደ ቤት ከመመለስዎ በፊት፣• እጅዎን በአግባቡ በሳሙናና በውሃ ሳይታጠቡ ዓይንን፣አፍንጫንና አፍን ባለመነካካት፣• የታመመ ሰው ካለ ባለመቅረብ ወይም የቅርብ ንክኪ ባለማድረግ እና ቢያንስ ሁለት የአዋቂ እርምጃ ያህል በመራቅ፤• ህዝብ በሚበዛበት አካባቢ ባለመሳተፍ፣• የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማግኘት ለምሳሌ ለታክሲ ወይም ለመድሃኒት ቤት ሰልፍ ላይ ተጠጋግቶ ባለመሰለፍ፣• በሚያስነጥሱበትና በሚያስሉ ጊዜ አፍና አፍንጫን በሶፍት ወይም በታጠፈ ክንድ በመሸፈን፣• የተጠቀምንበትንሶፍት ክዳን ባለው ዕቃ በአግባቡ በማስወገድ እንትጋ!ከምንም በላይ ደግሞ በየእምነታችን ወደ ፈጣሪያችን እንፀልይ!!ፈጣሪ ዓለማችንን እና ኢትዮጵያን በምህረቱ ያስብ!!አዱኛ ደበላ (ዶ/ር)የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር

Total Page Visits: 270 - Today Page Visits: 3
About The Author

Leave a reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *