የካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ 2021 ውድድር አሸናፊዎች ተለዩ!

የካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ 2021 ውድድር አሸናፊዎች ተለዩ!
May 31, 2021 No Comments News admin

ግንቦት 17/2013 ዓ.ም

ኢ/ቡ/ሻ/

የኢትዪጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ከአሜሪካን ተራድኦ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ እንቅስቃሴ/US AID-Feed The Future Ethiopia እንዲሁም ከኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር ጋር በመተባበር ሲያካሂደው የቆየው ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ የባለልዩ ጣዕም ቡና ጥራት ውድድር ወደ መጨረሻው ምዕራፍ እየተዳረሰ ሲሆን ምርጥ 30 አሸናፊ ቡናዎችም ተለይተዋል፡፡የውድድር አሸናፊዎቹ ውጤት ይፋ የተደረገው የኢትዪጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር አዱኛ ደበላ፣ ከአሜሪካን ተራድኦ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ እንቅስቃሴ/US AID-Feed The Future Ethiopia ፕሮግራም ዳይሬክተር ወ/ት ቅድስት ሙሉጌታ እንዲሁም የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር ፕሬዝደንት አቶ ደሳለኝ ጃና በጋራ በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል ለጋዜጠኞች በሰጡት የፕሬስ መግለጫ ላይ ነው፡፡ ዶ/ር አዱኛ በንግግራቸው መክፈቻ ላይ እንደ አምናው ሁሉ ዘንድሮ ከፊድ ዘ ፊዩቸር፣ ከቡና ላኪዎች ማህበር እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ስናካሂድ የቆየነው ውድድር በዳግም በብዙ ሪከርዶች ታጅቦ በፍጻሜው ላይ መድረሱን እና አምና ተስፋ እንደጣልነውም ከባለፈው አመት አሸናፊዎች ውጪ ሌሎች በርካታ በጥራት የበቁ አርሶ አደሮችንም ልናፈራ በመቻላችን ሁላችንም እንኳን ደስ ያለን ብለዋል፡፡ ውጤቱ የሁሉም ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረት በመሆኑም ሁሉንም በውድድሩ ሚና ለነበራቸው አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ለውድድር ከቀረቡት ቡናዎች መካከል 150 ለመጀመሪያው ዙር መመረጣቸውን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ ከነዚህ ውስጥ ደግሞ 30ዎቹ በውድድሩ 87 ነጥብ እና በላይ በማምጣታቸው አሸናፊ ሲሆኑ አምስት ቡናዎች ደግሞ ከ90 በለይ ውጤት በማስመዝገብ የፕሬዝደንሺያል አዋርድ የሚታወቀውን የውድድሩን ከፍተኛ እውቅና አግኝተዋል፡፡ እስካሁን ድረስ ከ7 ሀገራት 137 የሚሆኑ ገዢዎች የተመዘገቡ ሲሆን በመጪው ሰኔ 30/2013 ዓ.ም በአሊያንስ ፎር ኮፊ ኤክሰለንስ ድህረ ገጽ ላይ በቀጥታ የኢንተርኔት ግብይት ለ24 ሰዓታት በሚቆይ ጨረታ ለሽያጭ እንደሚቀርቡ ተናግረዋል፡፡ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ቡድን በቦታው ላይ ተገኝቶ ዘግቦታል!!

Total Page Visits: 85 - Today Page Visits: 1
About The Author

Leave a reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *