የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን የኢትዮጵያ ሚንስትሮች ምክር ቤት በመመሪያ ቁ. 364/2008 ባስተላለፈው ትእዛዝ መሰረት በኢትዮጵያ ግብርና ሚኒስተር ስር የቡና፣ ሻይ እና ቅመማ ቅመም ልማቱን ለመደገፍ፣ ለመርዳት እንዲሁም ለማሳደግ የተቋቋመ ተቋም ነው። ይህ ኢንደስትሪ ልዩ የሆነውን ተፈጥሮአዊውን የህዝብ ሃብት በእውቀት፣ በፈጠራ እና ኢንደስትሪ ልቀት በማሳደግ ይከናወናል።

የኢትዮጵያ መንግስት የዚህ ኢንደስትሪ ዘርፍ ልማት፣ የእሴት ሰንሰለቱን እና የሃገሪቱን ኢኮኖሚ በማሳደግ የህዝቡን የኑሮ ደረጃ በላቀ ሁኔታ ይቀይራል ብሎ ያምናል።

የግብዓት አቅርቦትና ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት

 

የቡና፣ ሻይና የቅመማ ቅመም የግብዓት አቅርቦትና ጥራት ቁጥጥር ዋና ስራ ሂደት ተጠሪነቱ ለቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ልማት ዘርፍ ሆኖ ዋና ተልዕኮው የምርት ማሳደጊያና ማዘጋጃ ግብዓቶችን፣ ማሽነሪዎችን፣ የምርት ማሸጊያዎችንና የጥራት መቆጣጣሪያ መሣሪያዎችን ለተገልጋዮች በጥራትና በተወዳዳሪ ዋጋ የሚቀርብበት፣ የግብዓት ጥራት ደረጃ ለመቆጣጠር የሚረዳ እንዲሁም የአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ብቃት በመስክ በማረጋገጥ ለአገልግሎት እንዲውሉ የሚለቀቁበት እና የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችና ግብዓቶች በተለያዩ አማራጮች ተባዝተው፣ተመርተው ወይም  ተገዝተው በወቅቱ ለተጠቃሚው በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርቡ የሚረጋገጥበት የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት ነው፡፡ ለተግባራዊነቱም አሰፈላጊውን ድጋፍና ክትትል የማድረግና ለግብዓቶች መግዣ የሚያገለግል የፋይናንስ አቅርቦት እና የማሽኖች ሊዝ ፋይናንሲንግ ለተገልጋዩ የሚቀርቡበትን ሁኔታ ያመቻቻል፡፡

Under read more section….

ከአደረጃጀቱ የሥራ ስፋትና ውስብስብነት እንዲሁም ተደራሽነትንና ውጤታማነትን ለማረጋገጥ እንዲያስችል በስሩ የሰብል ግብዓቶች ቡድን እና የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ቡድኖችን በዕጽዋት ሳይንስ፣ በሆርቲካልቸር፣ በዘር ሳይንስ፣ በምግብ ቴክኖሎጂ፣ በኬሚካል፣ ሜካኒካል፣ መስኖ እና ግብርና ምህንድስና እንዲሁም ሥራ አመራር ሙያዎች የተመረቁ ባለሙያዎችን በመያዝ ተደራጅቷል፡፡ የስራ ሂደቱ ዝርዝር ተግባርና ኃላፊነት  የሚከተሉት ይሆናሉ፡-

 1. የቡና፣ ሻይ እና ቅመማ ቅመም ሰብሎች ምርትና ምርታማነት ማሳደጊያና ጥራት ማሻሻያ ግብዓቶች አቅርቦትንና ጥራት ቁጥጥር ለማሳለጥ የሚረዱ የፖሊሲ ሀሳቦችን ያመነጫል፣ ስትራቴጂዎችን ይነድፋል፣ አዋጆችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን ያዘጋጃል፤ ሲፈቀድም በሥራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣ ይደግፋል፤ ይከታተላል፣
 2. አርሶ አደሮች፣ አልሚ ባለሃብቶች፣ ድርጅቶችና ማህበራት ፍላጐትና የዘርፉ ቀጣይ አቅጣጫ ላይ ተመስርቶ ዘርና ሌሎች ግብዓቶች/ቴክኖሎጅዎች አቅርቦትና ጥራት ቁጥጥር ላይ የአጭር፣ የመካከለኛና ረጅም ጊዜ ዕቅዶችን ያዘጋጃል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያድርጋል፣ አፈጻጸማቸውን ይከታተላል ሪፖርት ያቀርባል፣ ግብረ-መልስ ይሰጣል፤
 3. የአርሶ አደሮች የግብዓቶች/ቴክኖሎጅዎች ፍላጐትን በማሰባሰና በመተንተን ከአቅራቢ ድርጅቶች እና ማህበራት ጋር የማስተሳሰር እንዲሁም የብድር አገልግሎት የማመቻቸት ስራ ያከናውናል፣
 4. የቡና፣ ሻይ እና ቅመማ ቅመም ምርትና ምርታማነት ማሳደጊያና ጥራት ማሻሻያና ማምረቻ ግብዓቶች አቅርቦትና ጥራት ቁጥጥርን ለማሳለጥ ብሄራዊና ክልላዊ ስትራቴጂዎች፣ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ቀረጻ ላይ ይሳተፋል፤ የማስፈጸሚያ ዕቅድ ያዘጋጃል፤  ያስተባብራል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
 5. ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የቡና፣ ሻይ እና ቅመማ ቅመም ግብዓቶችን በሚፈለገው ዓይነት፣ መጠን፣ ጥራት፣ ቦታና ወቅት ለማቅረብ የሚያስችል ውጤታማ የሆነ የአሰራርና የመረጃ ሥርዓት በመዘርጋት ተግባራዊ ያደርጋል፣ ብቃትንና ጥራትን ያረጋግጣል፣
 6. ሥነ-ምህዳርን ማዕከል ያደረገ የቡና፤ ሻይና ቅመማ ቅመም ምርትና ምርታማነት ማሳደጊያ ግብዓቶች/ቴክኖሎጂዎች ብዜት፣ አቅርቦትና የግብይት ትስስር ላይ ለባለሙያዎች፣ ለአምራቾች፣ ለአቅራቢዎች እና ለተጠቃሚዎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ያደርጋል፣
 7. በዘርና ችግኝ ብዜት እንዲሁም የኢንዱስትሪ ግብአት አምራች አካላት የማሳ እና የመጋዘን የኢንስፔክሽን ስራዎች እንዲሁም የቡና፣ሻይና ቅመማ ቅመማ ዝርያዎች የማሳ ላይ ግምገማ ያከናውናል፣የውሳኔ ሃሳብ አዘጋጅቶ የሚመለከተውን ያሳውቃል፣
 8. በቡና፤ ሻይና ቅመማ ቅመም ምርትና ምርታማነት ማሳደጊያ ግብዓቶች/ቴክኖሎጂዎች ብዜት፣አመራረት፣ አቅርቦትና ስርጭት የተመዘገቡ መልካም ተሞክሮዎች ይሰበስባል፣ ይለያል፣ ይቀምራል፣ እንዲስፋፉ ያደርጋል፣ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፣
 9. በዘርፉ የወጡ እና ሀገሪቱ የተቀበለቸቸውን ዓለም አቀፋዊ፣ አሁጉራዊና ክልላዊ ትብብሮችና ስምምነቶችን ህጎችና በስራ ላይ ያውላል፣ ስለ አተገባበሩም ሪፖርት ያደርጋል፣
 10. ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋት ወቅቱ ከሚጠይቀው የምርት ማሳደጊያ ግብዓት/ቴክኖሎጅ ልየታ፣ ብዜት፣ አመራረት፣ አቅርቦትና ጥራት ቁጥጥር ጋር የተጣጣመ ሥርዓት ትምህርት እንዲቀረጽ ይደግፋል አፈጻጸሙን ይከታተላል፣
 11. የቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ምርት ለሚያዘጋጁና በእሴት ጭመራ/ አግሮ ፕሮሰሲንግ ሥራ ላይ ለተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች የሚያገለግሉ ግብዓቶች በተለይም ማሽነሪዎችን፣ የምርት ማሸጊያዎችንና የጥራት መቆጣጣሪያ መሣሪያዎችን በጥራት፣ ተወዳዳሪ በሆነ ዋጋ በግዥ፣ በብድር ወይም በሊዝ ፋይናንሲንግ የሚቀርብበትን የአሠራር ሥርዓት ይዘረጋል፣ ተግባራዊነቱን ይደግፈል፣
 12. ከሚመለከታቸዉ ተቋማት ጋር በመቀናጀት የዘርና የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ለቀቃ፣ አቅርቦትና ጥራት ቁጥጥርን ይበልጥ ለማጠናከር፣ በተግባር የሚታዩ ማነቆዎችን ለመለየትና ለመፍታት የሚያስችሉ ጥናቶችን ይመራል፤ ዉጤቶቹም ሥራ ላይ የሚዉሉበትን ስልቶች ያዘጋጃል፤ ሲፈቀድም አተገባበሩን ይከታተላል፤ ያስተባብራል፣
 13. በስሩ የሚገኙ ቡድኖችን የአቅም ግንባታ የለውጥና፣ የመልካም አስተዳደር ሥራዎች፣ የውጤት ተኮር ዕቅድና አፈጻጻም ይመራል በተቀመጠው መስፈርት መሠረትም ይገመግማል ደረጃ ያወጣል፣ ግብረ መልስ ይሠጣል፤
 14. የዘርና የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ለቀቃ፣ አቅርቦትና ጥራት ቁጥጥር ከሀገሪቱ የአየር ንብረት ለዉጥ መቋቋሚያ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ ጋር በተጣጣመ መልኩ እንዲከናወን ከሚመለከታቸው ባለድርሻዎች ጋር በቅንጅት ይሰራል፣
 15. ለክልሎች በተለይም ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ክልሎች የግሉ ዘርፍ ባለሙያዎች በግብዓት አቅርቦትና ጥራት ቁጥጥር ዙሪያ የሥልጠናና የምክር ድጋፍ ይሰጣል፤ የዘርፉ ሠራተኞችን ዕውቀትና ክህሎት ለማጎልበት የሚረዱ የሥልጠናና የሙያ ማሻሻያ ስልቶችን ይቀይሳል፣ሲፈቀድ ይተገብራል፣
 16. ለተገልጋዮች ጥያቄና ቅሬታ ወቅታዊ ምላሽ ይሰጣል፣ የእርምት እርምጃ ይወስዳል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣
 17. የባለሥልጣኑን ዓላማና ግብ ለማሳካት እንዲያስችል የሥራ ሂደቱን ዕቅድና የአፈጻጸም ሪፖርት ያዘጋጃል፣ ውጤታማነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል የአሰራር ማሻሻያ ጥናት ያደርጋል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፣
 18. የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማስፋፋትና ለማሳለጥ አጋዥ የሆኑ የፕሮጄክት ሀሳቦችን ያመነጫል፣ ፕሮፖዛሎችን ያዘጋጃል፣ የፋይናንስ ምንጭ ያፈላልጋል፣ ሲገኝም ሥራ ላይ ያውላል፣
 19. ለስራ ሂደቱ የተመደበውን በጀት ያስተዳድራል፣ ዉጤታማነትን በሚያረጋግጥ አግባብ ስራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፤

 

 

Shopping Cart