የሚድሮክ ሊቀ-መንበር ሸህ መሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ፣ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ፣ የሚድሮክ አመራሮች፣ ሰራተኞች፣ ቤተሰቦችና ደንበኞች እንኳን ደስ ያለን! እንኳን ደስ አላችሁ!!!
የ2014 የቡና ቀን የሚድሮክ ቀን ሆኖ አልፏል፡፡ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚም ወደ መድረኩ በተደጋጋሚ ጊዜ በመጠራት በታዳሚው ዘንድ አድናቆት ተችሯቸዋል፡፡ ሚድሮክ ሊወዳደርባቸው በቻሉ ዘርፎች ሁሉ አሸናፊ ሆኗል፡፡
በአጭሩ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የቡና ቀን ሽልማትን በሸራተን አዲስ ሆቴል ተቆጣጥሮት ውሏል፡፡
ቀጥሎ በቪዲዮው ላይ እንደምትመለከቱት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ ለ9 ጊዚያት ያህል ተመላልሰው ሽልማቱን ከክብርት የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት እጅ ተቀብለዋል፡፡
በዚህ አስደናቂ ክስተት የታዳሚውን አፍ አስከፍቷል፡፡
ዋንጫ፣ ሜዳሊያ እና ሰርተፍኬት ያገኘንባቸው ዋና ዋና ዘርፎችም ቀጥሎ ተዘርዝረዋል፡፡
* ከፍተኛ ገቢ ያስገኙ የቡና አልሚ ላኪዎች ሽልማትን
* የቡና ማዘጋጃና ማከማቻ ኢንደስትሪዎች ሽልማትን
* ከፍተኛ ገቢ ያስገኙ የቅመማቅመም አልሚ ላኪዎች ሽልማትን
* ከፍተኛ ገቢ ያስገኙ የሻይ ምርት ላኪዎች ሽልማት እና
* የልዩ ተሸላሚ ሽልማት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የዝግጅቱ የፕላቲኒየም ደረጃ ስፖንሰር ከመሆን ባለፈ የቡና አብቃይ ለሆኑ 5 ክልሎች 50 በእጅና በነዳጅ የሚሰሩ የእሸት ቡና መፈልፈያ ማሽኖችንም በስጦታ አበርክቷል፡፡
Add a Comment