photo1698084178

በቡና ሙያ የሰለጠኑ የሞዛምቢክ ዜጎች ተመረቁ!!

ጥቅምት 09/2016 ዓ∙ም
ኢ/ቡ/ሻ/ባ
በባሬስታ በቅምሻ እንዲሁም በሌሎች መሰረታዊ የቡና ሙያዎች ላይ ስልጠናቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ከሞዛምቢክ የመጡ ዜጎች በዛሬው እለት ተመርቀዋል:: እነዚህ ሰልጣኞች በሞዛምቢክ በተለያየ የስራ ሃላፊነት፣ በቡና ማልማት እንዲሁም ሌሎች ከእሴት ሰንሰለቱ ጋር በተያያዘ ንቁ ተሳትፎ ያላቸው መሆናቸው ታውቋል:: ከእነሱ በተጨማሪ በአገር ውስጥ ከተለያዩ ትልልቅ የቡና ካምፓኒዎች፣ ማህበራት፣ ተቋሞች እንዲሁም በግል ስልጠናውን ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎችም ሊመረቁ ችለዋል::


በተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ተቋም/UNIDO ዳይሬክተር ሚስ አውሮሊያ ፔዚሪያ በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተው ለተመራቂዎቹ ሰርቲፊኬት ከሰጡ በኋላ እንደተናገሩት በዩኒዶ የገንዘብ ድጋፍ የተገነባው ይህ ማእከል በአጭር ጊዜ ውስጥ በቡና ዘርፍ ላይ አዳዲስ ባለሙያዎችን በማፍራት በኩል ትልቅ አስተዋፅዖ እያደረገ መሆኑ እንዳስደሰታቸው እና አሁን ደግሞ ከአገር ውስጥ በተጨማሪ ሰልጣኞችን ከአገር ውጪም እየተቀበለ ማሰልጠን መጀመሩ ለዘርፉ እድገት ከፍተኛ እመርታ መሆኑን አስረድተዋል:: ይህ ከመደበኛ ትምህርት በተጨማሪ የልምድ ልውውጥ እንዲኖር እገዛ ያደርጋል ነው ያሉት ሚስ አውሬሊያ:: ሞዛምቢክን መሰል በቡና ማልማት በኩል ገና ታዳጊ የሆኑት አገሮች ዘርፉን መቀላቀላቸው ወደፊት የቡናውን እድገት ፈጣን ሊያደርገው የሚችል እና ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን ጠቁመዋል:: መሰረታዊ የሆኑ የባሬስታ ቅምሻ እና መቁላት ስልጠናዎች በተጨማሪ የቡና ፓኬጂንግ ቴክኖሎጂ እና የገበያ ስትራቴጂዎችን መስጠት መቻሉ የስልጠና አይነቶችን ምን ያህል እየሰፉ መሄድ እንደቻለ የሚያሳይ ሲሆን በቡና ላይ ጥሩ ልምድ ያላት ኢትዮጵያ ከሞዛምቢክ ሰልጣኞች ጋር በቅንጅት መከናወን መቻሉ የበለጠ አስደሳች መሆኑን ተናግረዋል:: ከሌሎች አገራትም ሌሎች ሰልጣኞች እንደሚኖሩ ተስፋቸውን የገለጹት ሚስ አውሬሊያ ዩኒዶ ፣ ኢሊ ካፌ እና ሌሎች ትልልቅ ተቋማት ጋር በመቀናጀት የሚያደርጉትን አስተዋፅዖ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስረድተዋል::
ክቡር ዶክተር አዱኛ በበኩላቸው ዩኒዶ በየጊዜው ለሚያደርጋቸው ያላሰለሱ ድጋፎች በኢትዮጵያ መንግስት እና በባለስልጣን መስሪያ ቤታቸው ስም የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበው ከኢትዮጵያውያን በተጨማሪ የሌሎች አገር ዜጎችም በዚህ የቡና ማሰልጠኛ ስልጠናዎችን መውሰድ መጀመራቸው ማእከሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ እና አፍሪካውያንን በቡና የማስተሳሰር እና የተለያዩ ልምዶችንም በመለዋወጥ የቡና ኢንዱስትሪውን ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ እንደሚቻል አመላካች እንደሆነ ተናግረዋል::
ከሞዛምቢክ የመጡት ሰልጣኞችም በነበራቸው ቆይታ በርካታ እውቀቶችን መጨበጥ መቻላቸውን ገልጸው ወደ አገራቸው ሲመለሱም የቀሰሙትን እውቀት ወደ ተግባር እንደሚለውጡ አስረድተዋል::

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *