photo1698084040

የግብርና ሚኒስትሩ ባለስልጣን መ/ቤቱን ጎበኙ!! ከበላይ አመራሩ እና የማኔጅመንት አባላትም ጋር መክረዋል!!

ጥቅምት 07/2016 ዓ.ም
ኢ/ቡ/ሻ/ባለስልጣን

ክቡር የኢፌዲሪ ግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ግርማ አመንቴ ዶ/ር በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋናው መ/ቤት በመገኘት የተቋሙን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ በእድሳት ላይ የሚገኘውን እና በከፊል ተጠናቅቆ ስራ የጀመረውን የህንፃ አጠቃላይ ገጽታ እና ዘመናዊ ቢሮዎች የተመለከቱ ሲሆን በዩኒዶ እና በባለስልጣን መ/ቤቱ ትብብር ተገንብቶ በስራ ላይ የሚገኘውን የቡና ማሰልጠኛ ማዕከልም ጎብኝተዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትሩ የህንጻው በዘመናዊ ሁኔታ መታደስ ለተገልጋይም ሆነ ለባለስልጣን መ/ቤቱ ሰራተኞች ጥሩ የስራ መንፈስን የሚፈጥር እና ለደንበኞችም የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት ያለው ሚና ወሳኝ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ በቡና ማሰልጠኛ ማዕከሉን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ እና በስልጠና ላይ የሚገኙትን ሰልጣኞች ተዘዋውረው የተመለከቱት ክቡር ሚኒስትሩ ማዕከሉ ለቡና ኢንደስትሪው ማደግ እና በዘርፉ ይታይ የነበረውን የሰለጠነ ባለሙያ ክፍተት ከመቅረፍ አይነተኛ አስተዋጽዖ ሊያደርግ እንደሚችልም ነው የጠቆሙት፡፡ በወቅቱ በስልጠና ላይ ከሚገኙ ሰልጣኞች መካከል ከሞዛምቢክ የመጡ ሰልጣኞችንም ክቡር ሚኒስትሩ አጠቃላይ የስልጠና አሰጣጡን በተመለከተ ቀርበው አነጋግረዋቸዋል፡፡
ከጉብኝቱ በኋላ ክቡር ሚኒስትር ዶ/ር ግርማ አመንቴ ክቡር ዶ/ር አዱኛን ጨምሮ ከመ/ቤቱ የበላይ አመራሮች እና የማኔጀመንት አባላት ጋር ሰፋ ያለ ውይይትም አካሂደዋል፡፡
ከውይይቱ ቀደም ብለው ክቡር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ የመ/ቤቱን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ፣ በመንግስት ከተሰጠው ኃላፊነት አንጻር ባለስልጣኑ የሚያከናውናቸውን ስራዎች፣ ከቡና፣ ሻይ እና ቅመማ ቅመም ልማት፣ የኤክስቴንሽን እና ምርምር ስራዎች እንዲሁም ከግብይት ስራዎች ጋር በተያያዘ የወጡ ደንብ፣ መመሪያ እና ማንዋሎች ዙሪያ ማብራሪያዎችን አቅርበዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በሶስቱም ዘርፎች የተገኙ የኤክስፖርት አፈጻጸሞችም ላይ በቂ ገለጻ ያቀረቡ ሲሆን በወደፊት ዕድሎች እና ተግዳሮቶችም ላይ ሰፊ ትንታኔ ሰጥተዋል፡፡

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *