4

ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ ውድድር ለማካሄድ የሚስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ!!

ጥር 18/2016 ዓ.ም

የባለልዩ ጣዕም ቡና ቅምሻ ውድድር/ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ በኢትዮጵያ ለማካሄድ የሚስችል የመግባቢያ ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈርሟል፡፡ የመግባቢያ ስምምነት ሰነዱ ተፈረመው በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን፣ በኢትዮጵያ ብሄራዊ የቡና ማህበር እንዲሁም በአሊያንስ ፎር  ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ መካከል ነው፡፡

ስምምነቱን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በኩል የፈረሙት ክቡር ዶ/ር አዱኛ ደበላ የባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ሲሆኑ ክቡር ዶ/ር ሁሴን አምቦ  የኢትዮጵያ ብሄራዊ የቡና ማህበር ቦርድ ፕሬዝደንት እንዲሁም በአሊያንስ ፎር  ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ በኩል ደግሞ ሚ/ር አርዊን ናቸው፡፡

ውድድሩ በአገራችን ለሁለት ተከታታይ ጊዜያት መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን በርካታ የቡና አርሶ አደሮችን በአፍታ ሚሊየነር ያደረገ እንደነበር አይዘነጋም፡፤ በተለያዩ ምክንያቶች ውድድሩ በባለፈው አመት ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም በዘንድሮ አመት ግን ውድድሩን በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ ውሳኔ ላይ እንደተደረሰ ክቡር ዶ/ር አዱኛ ደበላ ገልጸው፤ አርሶ አደሩ ልክ እንደከዚህ ቀደሙ ቡናውን ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ መሰብሰብ እና ማዘጋጀት እንደሚገባው እና ራሱንም ለዚህ ከፍተኛ ውድድር እንዲያዘጋጅ ጥሪ ቀርቦለታል፡፡  

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *