w5.2

የዓለም የሴቶች ቀን በኢትዮያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ሠራተኞችና አመራሮች ተከብሮ ዋለ

መጋቢት 28/2016
ኢቢሻባ
በስራ  እንቅስቃሴ  የላቀ ክንውን ላሳዩና በነጥብ ደረጃ ላገኙ ሴት የባለስልጣኑ ሠራተኞችና አመራሮች የእውቅና ስነስርዓት ተካሄደ
የኢትዮያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በየዓመቱ ሲያከናውነው እንደመጣው ሁሉ ዘንድሮም ‹‹ሴቶች ላይ ኢንቨስት ማድረግ እድገትን ማፋጠን›› በሚል መሪ ቃል የሴቶች ቀን በማረ ዝግጅት አክብሮ ውሏል፡፡ በዝግጅቱ መጀመሪያ ላይ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣን መስሪያቤቱ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ የሆኑ አቶ ፍጹም መንገሻ ሲሆኑ በንግግራቸው አጠቃላይ የሴቶች ቀን አጀማመርን ያነሱ ሲሆን አሁን ድረስ ለመከበሩ ምክንያት የሆኑ ነጥቦችንም ዘርዝረዋል፡፡

አያይዘውም በሴቶች ላይ እየደረሰ ያለው በደል አሁን ድረስ የቀጠለ በመሆኑ አሁንም ቀኑ እንዲከበር አድርጎታል ብለዋ፡፡ በዓሉ የሚከበረው በደልን ለመዘከር ብቻ ሳይሆን ይህን ተቋቁመው በተለያዩ የዘርፎች ያገኙትን ትሩፋቶችን ለማውሳትም ነው ያሉ ሲሆን የክብረባዓሉ መሰረቱ ፓለቲካዊ ዓመፅ እንደሆነ እንዲሁም በአሁኑ ሰዓት በሴቶች ላይ ያለው የተዛባ የሰርዓተ ጾታ ሃይል ሚዛንን ለማስተካከል በተለያዩ ተግባራት እንደሚከበር አውስተዋል፡፡


በማስከተልም የሕይወት ተሞክሯቸውን እንዲያካፍሉ ከሰብኣዊ መብት ኮሚሽን  ባለሞያ የሆኑት ወ/ሮ አትክልት ፈጠነ በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ያላቸውን የሕይወት ተሞክሮ አካፍለዋል፡፡ ይህ እድል ስለተሰጣቸው ካመሰገኑ በኋላ እንደ አካላ ጉዳተኛ ያላቸውን ተሞክሮ ሲያወሱም ዋናው የአካል ጉዳተኛ ችግር የአካላ ጉዳተኛ መሆኑ ሳይሆን ይህን ተቋቁሞ ለለውጥ በሚደረግ ጥረት የሚያጋጥሙ የተለያዩ ተግዳሮቶች ናቸው ችግር የሆኑብን ሲሉ አሳስበዋል፡፡ እንደምሳሌ በተደጋጋሚ ያነሱትም እንደሰራተኛ ለሚሰራም ሆነ ተገልጋይ ሆኖ ለሚመጣ አካል ጉዳተኛ የስራ፣ የንግድ፣ የጤና ቦታዎችና ተቋማት ምቹ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ከቃላት አጠቃቀም ጀምሮ አካል ጉዳተኞችን እምንገልጽባቸው መንገዶች ላይ ጥንቃቄ  እንደያስፈልግ አሳስበዋል፡፡ በኢትዮጵያ 20 ሚሊዮንና ከዛ በላይ የአካል ጉዳተኞች እንዳሉ ይገመታልም ብለዋል፡፡ ይህ ማለት ከሁለቱ በሕዝብ ብዛት ከሚበልጡ ብሔረሰቦች ቀጥሎ ያለ የሕዝብ ቁጥር ብዛት ማለት ነው ሲሉ አጽንኦት ሰተውበታል፡፡ ‹‹ከአካል ጉተኛ ደግሞ ሴት አካል ጉዳተኛ ሲኮን ጫናው ከበድ ያለና ተደራራቢ ያደርገዋል›› ብለዋል፡፡


በክብረበዓሉ ከቀረቡት ዝግጅቶች አንዱ በሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ክፍል ባለሞያ የሆነችው ወጣት ጽገ ገ/ኪዳን ስትሆን በድንቅ አቀራረብ በፓወር ፖይንት የታገዘ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ሴቶች ላይ ያጠነጠነ ሰነድ አቅርባለች፡፡ ባቀረበችው ፓወር ፖይንትም ከቀደሙት ዘመናት ጀምሮ እስካለንብት ድረስ ያለውን የኢትዮጵያ ሴቶች ተግዳሮቶችን፤ በአንጻሩ ደግ  እየታዩ ያሉ ለውጦችን አሳይተዋል፡፡  በተጨማሪም ከቀደምት ዘመናት ተጽእኖ ፈጣሪ በመሆን ከሚታወቁ እንስት ኢትዮጵያውያን አንዷ የሆኑትን እቴጌ ምንትዋብን አንስታለች፡፡ በነበራት የሰነዱ አቀራረብ ሁኔታም ከነበረው ታዳሚ ከፍ ያለ አድናቆት ተችሯታል፡፡ መሰል እድሎችን ለሴቶች በመስጠት የሴቶችና ማኅበራዊ ጋዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ፍጹም መንገሻ ምስጋናና አድናቆት ከታዳሚው ተችሯቸዋል፡፡ ባቀረበችው ሰነድ ላይ ውይይት ተካሂዶበት በርካታ ጠቃሚ ነጥቦች ከታዳሚው ተሰንዝረዋ፡፡
በዝግጅቱ ወቅት የባለስልጣን መስሪያቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ክፍልም የበኩሉን ዝግጅት ያቀረበ ሲሆን በዝግጅቱም ከጥንት ጀምሮ አስካለንብት ዘመን በኢትዮጵያ ታሪክ ተጽእኖ ፈጣሪና ለውጥ አምጪ ሆነው ያለፉትን ሴቶችን አስመልክቶ በጥናት ተደግፎ የተዘጋጀን ሰነድ አቅርቧል፡፡ የሰነዱ መቅረብ ዋና ዓላማም መሰል ሴቶችን ስራቸውንና ማንነታቸውን ማወቅና ማውሳት ለይቻላል መንፈስና ሞራል ግንባታ ወሳኝ ነው ስለሆነ ነው ተብሏል፡፡ በሕይወት ዘማነችንም እነዚህን ሴቶች በየጊዜው ማንሳት ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተወስቷል፡፡
በስተመጨረሻም በባለስልጣን መስሪያቤቱ የመስሪያቤቱን ራዕይ ተልዕኮ አውቆ ስራን በላቀ ሁኔታ በማከናወን ለሚታወቁ ሴት የስራ ኃላፊ እና ሠራተኛ የእውቅና ስነስርዓት ተካሂዷል፡፡ በዚህም በኃላፊ ቦታ ዘርፍ ያሸነፉት ወ/ሮ ሽቶ ተስፋዬ የገበያ ልማትና ድጋፍ ዴስክ ኃላፊ ሲሆኑ በታታሪ ሰራተኛ ዘርፍ ደግሞ ወ/ት እስከዳር ሽኩር የአይ ሲ ቲ ባለሞያ ናቸው፡፡ የምርት ጥራት ምርመራና ሰርትፊኬሽን ማዕከል ደግሞ ለብቻ የተወዳደሩ ሲሆን በታታሪ ሰራተኛ ዘርፍ ደግሞ ወ/ሮ ጽጌ ዎርዶፋ አብላጫውን ድምጽ አግኝተዋል፡፡ በሴት ኃላፊ ዘርፍ ምርጫ የተካሄደው በስራ አስፈጻሚ፣ ዴስክ ኃላፊና ቡድን መሪ መደቦች እንደሆነ ከአዘጋጅ ክፍሉ መረዳት ተችሏል፡፡

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *