3

የቻይና የመንግስትና የንግዱ ማህበረሰብ ቡድን ከኢትዮጵያ ቡና ላኪ ድርጅቶች እና ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ጋር በመገናኘት በቡና ኬክስፖርት ዙሪያ ውይይት አካሄደ፡

ታኅሳስ 08/2016

ውይይቱን ያስጀመሩት ክቡር ዶክተር አዱኛ ደበላ የኢትዮጵያ ቡና፣ ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሲሆኑ ለልምድ ልውውጥና በቡናው ንግድ ጥናት አድርጎ በስራው ለመሰማራት ከቻይና ለመጣው ኢንቬስትመንትና ንግድ ቡድን የኢትዮያ ቡና ከምርቱ እስከ ኤክስፖርቱ ያለውን ሂደት ገለጻ አድገዋል ፡፡ አያይዘውም ኢትዮጵያ በዓመት ወደ 8 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ቡና ወደ ውጭ እንደምትልክ ገልጸዋል፡፡ እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር በ2023 የመጨረሻዎቹ አራት ወራት ውስጥ 5285 ቶን ቡና ወደ ውጭ መላኩን ለቡድኑ ጠቁመዋል፡፡ አያይዘውም የኢትዮጵያ ቡና አስር ዋና ዋና የአለም መዳረሻ አገራትን ጠቁመው ቻይና ከአስሩ የቡና መዳረሻዎች ስምንተኛዋ መሆኗን ጠቅሰዋል ፡፡

የቻይና ልዑክ ቡድኑ ከኢትዮጵያ የቡና ላኪዎች ባለሃብቶች የአሰራር ተሞክሮ በመውሰድ የኢትዮጵያን ቡና ተረክቦ ወደ ቻይና ለመላክ እና በቡናው የውጭ ንግድ ባለድርሻ ሆኖ ወደ ስራው ለመግባት አላማ ያለው መሆኑ በቡዱኑ ተወካይ ተገልቷል ፡፡

የኢትዮጵያ ቡና ላኪ ድርጅቶችም ያላቸውን የቡና መላክ ልምድና ይዘት ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡ ቻይና ካላት የሕዝብ ቁጥር አንጻርና ያደገ ኢኮኖሚ ያላት መሆኗ ተስፋ የሚጣልባት የቡና ገበያ እንደምትሆን ሙሉ ተስፋቸውን ገልጸዋል፡፡ በገለጻቸውም ከቻይና ጋር ያላቸውን የንግድ ትስስር ምን እንደሚመስል ያብራሩ ሲሆን ከማብራሪያቸው መረዳት እንደቻልነው በዓመት በአማካይ አስከ 700 ኮንቴይነር ቡና ወደ ዓለም ገበያ እንደሚላክ ለማወቅ ችለናል፡፡ ከቻይና ጋ ብቻ በቡና ንግድ ስራው ለሰባት ዓመታት ያክል የቆዩ ላኪ ካምፓኒዎች እንዳሉ ተገልቷል፡፡ ሆኖም ግን ከቻይና አንዳንድ ካምፓኒዎች የክፍያ አፈጻጸም ሁኔታ ላይ ግን ችግር እያጋጠማቸው እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡ በብዛት ሲ ኤ ዲ የተሰኘ የአከፋፈል ስርዓት ቻይና ካምፓኒዎች እንዲሚመርጡ ተገልቷል፡፡ በስተመጨረሻም ቻይናዎቹ ስለመጡና የኢትዮጵያ ቡና ላይ ከፍተኛ ፍላጎት ማሳደራቸውን አድንቀው አመስግነዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ኤክስፖርተሮቹ ገለጻ በኋላ ከቻይና የመጣው ቡድን የመሩት የቻይና ኢትዮጵያ ወዳጅነትና ትብብር ማኅበረሰብ ሴክሬታሪ ጀነራል የሆኑት ሚስተር ሺ ፊንጅ ሃሳባቸውን የገለጹ ሲሆን በኢትዮጵያ ላኪዎች በኩል ለተነሱት ችግሮችና ቅሬታዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ እንዳሉትም ‹‹ኢትዮጵያ ለገበያ የምታቀርባቸውን ሃብቶቿን ለመግዛት ከፍተኛ ፍላጎት አለን እናንተ ደግሞ የውጭ ምንዛሪ እጥረትና የቴክኖሎጂ ችግር እንዳለባችሁ ተገልጾልናል፤ ስለሆነም እኛ እነዚህን ችግሮቻችሁን ለመቅረፍ እንጥራለን እናንተ ደግሞ በምንፈልገው መጠንና ጥራ ምራታችሁን እያቀረባችሁ በንግዱ ዘርፍ እንተጋገዛለን›› ብለዋል፡፡ ቻይና እጅግ ብዛት ያለው ቡና ስለምትፈልግ ከፍተኛ መጠን ያለው ቡና ለመግዛት ዝግጁነታቸውን ገልጸዋል፡፡ ለዚህም ነው ይህ የውይይት መድረክ እንዲዘጋጅ የፈለግነው ብለዋል፡፡ ከቻይና ካምፓኒዎች ክፍያ አንጻር ለተነሳው ችግርም መልስ ሲሰጡ ችግሩን ከመሰረቱ ለመቅረፍ እንችላለን ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የተቋቋመ ድርጅት እንዳለና በኢትዮጵያና በቻይና መካከል ያለውን የንግድ ትስስር የሚያመቻች እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም የጸደቀ አክሽን ፕላን እንዳለና ፌዞች እንዳሉት፤ በመጀመሪያው ፌዝ 10 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንደተበጀተለት፤ ነገሮች በጥሩ ሁኔታ ከቀጠሉ ቀጣይ ፌዞችም ማስቀጠል እንደሚቻል አስረድተዋል፡፡

በስተመጨረሻም የእነሱ ሚና ቡናውን ከኢትዮጵያ ከገዙ በኋላ የቻይና ሀገር ውስጥ ገበያ ላይ መሸጥ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻ በኤ ኤም ጂ ቡና ላኪ ድርጅትና በኢትዮ ቻይና ወዳጅነትና ኮኦፐሬሽን ኮሚዩኒቲ ዘንድ በቡና መላክና መግዛት ዙሪያ ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን ከኤ ኤም ጂ በኩል ፊርማ ቸውን ያኖሩት የድርጅቱ መስራችና ኃላፊ የሆኑት አቶ አብዱልሃኪም መሐመድ ሲሆኑ ከኮምዩኒቲው በኩል ደግሞ ሚስተር ሺ ፊንጅ ነበሩ፡፡ በፍርርሙ ወቅት እንደተገለጸውም በ6 ወር ውስጥ በኮንቴይነር ከ450 በላይ፣ በዶላር ሲሰላ ደግሞ ከ50 ሚሊዮብ ዶላር በላይ ቡና ኮሚዩኒቲው ለመግዛት፤ ላኪ ድርጅቱ ደግሞ ለመላክ ስምምነት ላይ እንደተደረሰ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከስምምነቱ መረዳት እንደተቻለው ስፔሻሊቴ 2 አንደኛ ደረጃ፣ ሊሙ እና ሲዳማ 2 ቡናዎች ለመላክ እንደታሰበ ተገልጸዋል፡፡

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *