D6

ኢትዮጵያ የቡና ምርትና ምርታማነቷን በማሳደግ በዓለም ገበያ የተሻለ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያግዛት የምርምር ማዕከል ግንባታ በቅርቡ ሊጀመር ነው።

ኢ∕ቡ∕ሻ∕ባለስልጣን

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን እንዲሁም ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡና ማኅበር ጋር በመተባበር “የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ለኢትዮጵያ ቡና ኢንዱስትሪ ሽግግር” በሚል መሪ ቃል 4ኛውን ሀገር አቀፍ የቡና ሲምፖዚዬም አካሂዷል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘም በይርጋ ጨፌ ከተማ ለሚገነባው የቡና ምርምር ማዕከል ግንባታ የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃ ግብር የተካሄደ ሲሆን ከ900 ሚሊየን ብር በላይ ሊሰበሰብ ችሏል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዚሁ ጊዜ፤ ኢትዮጵያ ለቡና ልማት የተመቸ ተፈጥሮ ያላት ቢሆንም የዘርፉን ምርታማነት በማሳደግ የሚገባትን ያክል ተጠቃሚ አይደለችም ብለዋል።

የሀገሪቱን የዘርፉ ተጠቀሚነት ለማረጋገጥ የቡና አመራረትና የግብይ ሥርዓቱን ማዘመን እንዲሁም ዕሴት መጨመር እንደሚገባ ጠቅሰው ለዚህም ብቁ ባለሙያ ማፍራት ይገባል ካሉ በኋላ ይህን በማድረግ በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ መሆን እንደሚቻል ጠቁመዋል።

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትርና የዲላ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢ ክብርት ወ∕ሮ ጫልቱ ሳኒ በበኩላቸው፤ ከቡና ምርጥ ዘር ዝግጅት እስከ ግብይት ያለው ሂደት በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ በሚያደርግ አሰራር መመራት ይገባዋል ብለዋል።

የፌዴራል ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አዱኛ ደበላ(ዶ/ር) እንደተናገሩትም  ኢትዮጵያ በዓለም በቡና ምርት ያላትን ደረጃ ለማስጠበቅ የተወዳዳሪነት አቅሟን መገንባት አለባት ብለዋል። ይህንንም እውን ለማድረግ በዘርፉ ምርምር በማድረግ ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር እንዲሁም እሴትን የሚጨምር የልህቀት ማዕከላት መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል።

ይህንንም ከግምት በማስገባት ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የቡና ምርምር ማዕከል በይረጋጨፌ ለመገንባት አሁን ላይ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን አስረድተዋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ችሮታው አየለ(ዶ/ር)፤ ዩኒቨርሲቲው የቡና ልማትን በመማር ማስተማር እንዲሁም በምርምር ሥራዎች ውስጥ በማካተት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

አሁን ደግሞ ዘርፉን ማጠናከር የሚያስችል የቡና ምርምር ማዕከል በይርጋጨፌ ሊያስገነባ መሆኑን ገልጸው ግንባታው ለሚያርፍበት መሬት የካርታ ርክክብ መካሄዱን ጠቅሰው የምርምር ማዕከሉ ግንባታም በቅርቡ እንደሚጀመርም ጠቁመዋል።

በሲምፖዚየሙ ላይ ክቡር ዋና ዳይሬክተር ዶ∕ር አዱኛ ደበላ አጠቃላይ የቡናን ሁኔታ እና የደረስንበትን ደረጃ በተመለከተ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን የተለያዩ የቡና ምሁራንም ጋር የፓናል ውይይት ተካሂዷል

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *