moza 2

ከሞዛምቢክ ለመጡ የቡና ዘርፍ ባለሞያዎች ሁለተኛ ዙር ስልጠና መሰጠት ተጀመረ

መጋቢት 07/2016

ኢ/ቡ/ሻ/ባ፣

የኢትዮጵያ ቡና ሻይ ባለስልጣን የቡና ማሰልጠኛ ማዕከል በተለያዩ ጊዜያት ከተለያዩ የዓለማችን ክፍል ለመጡ ሰልጣኞች በባሬስታ፣ በቅምሻ እና በቡና መቁላት ዙሪያ ስልጠና ሲሰጥ እንደቆየው ሁሉ በዛሬው እለትም ከሞዛምቢክ ለመጡ አስራ ሁለት ሰልጠኞች ስልጠናዎቹን መስጠት የጀመረ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ አራቱ ሴቶች ናቸው፡፡፡ ከስልጠና ማዕከሉ ባገኘነው መረጃ መሰረት እነዚሁ ሰልጣኞች ከዚህ በፊት በሶስቱም ዘርፎች ስልጠና የወሰዱ መሆናቸውን እና በዚህ ሁለተኛ ዙር ስልጠና በቅምሻና ቡና መቁላት ላይ አጽንኦት ሰጥተው ስልጠናውን ለመውሰድ የመጡ መሆናቸው ታውቋል፡፡

ከስልጠናው መጀመር በፊት በተደረገው የእንኳን ደህና መጣችሁ ስነስርዓት ላይ ዩኒዶን በመወከል እና ከዚህ በተጨማሪ የአግሮኖሚ እና ቡና ጥራት ስልጠና ለመስጠት የተገኙት ዶ/ር ካሳዬ ቶሎሳ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ በቡና ሻይ ባለስልጣን የኢዩ ካፌ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ፍቅሩ አመኑም ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገዋል፡፡

አቶ ፍቅሩ በንግግራቸውም ሞዛቢክ በቅርቡ በቡና አለው ላይ መሰማራት የጀመረች አገር እንደሆነች፤ ይህንም ተገንዝቦ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባለው አቅም ለማገዝ ዝግጁ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ በማስከተልም በተቋም ደረጃ የኢትዮጵያ የኋላ ታሪክ በአጭሩ ገልጸው ከ1950ዎቹ ጀምሮ ተቋማዊ የቡና ዘርፍ እንቅስቃሴ እንደጀመረና የረጅም ጊዜ ተቋማዊ የቡና አመራር ልምድ እንዳለ አብራርተዋል፡፡ ስለሆነም ልምዶቹን በማካፈል ረገድ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ደስተኛ እንደሆነ ገልጸው በዚህ ስልጠና ማዕከልም በዋናነት በሶስቱ ዘርፎች ማለትም በቡና መቁላት፣ በቡና ቅምሻ እና በባሬስታ ዘርፎች እውቀትና ክህሎቱን እንዲቀስሙ እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡ ስለማሰልጠኛ ማዕከሉ ገለጻ ሲያረጉም ከአመሰራረቱ ጀምሮ ያለውን በአጭሩ አብራርተው በአመሰራረቱ ባለስልጣን መስሪያቤቱ፣ የዩኒዶና የጣሊያን የልማት ኮኦፐሬሽን አካላት ሚና ከፍተኛ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *