photo1698084260 (6)

ሚኒስቴር ዴኤታው የባለስልጣን መ/ቤቱን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ጎበኙ!

ጥቅምት 09/2016 ዓ∙ም
ኢ/ቡ/ሻ/ባ
የኢፌዲሪ ገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታው ክቡር ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴውን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል:: ሚኒስትር ዴኤታው በእድሳት ላይ የሚገኘውን የህንፃ ክፍል እንዲሁም ተጠናቆ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኙትን ዘመናዊ ቢሮዎች እና መሰብሰቢያ አዳራሾች ተመልክተዋል:: ከዚህ በተጨማሪ የቡና ማሰልጠኛው እያከናወነ ስለሚገኘው አገልግሎትም ክቡር ዶ/ር አዱኛ በዝርዝር አስረድተዋቸዋል:: ከጉብኝቱ በኋላ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የማኔጅመንት አባላት ጋር አጭር ቆይታ አድርገዋል::

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *