2

በቡና ጥራት ማኔጅመንት ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ!

(ጥር 2016 ዓ.ም፡ ኢ/ቡ/ሻ/ባ)፡-

በኢትዮጵያ ቡና አልሚዎችና ላኪዎች ማህበር(ECGPEA)፣በዩናይትድ ስቴትስ የግብርና ዲፓርትመንት(USDA) እና በቴክኖሰርቭ (Techno serve) ትብብር በኢንተርኮንቲነታል ላግዠሪ ሆቴል የተዘጋጀው ስልጠና በቡና ጥራት ማኔጅመንት ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡

አቶ መስፍን ደበሳ የኢትዮጵያ ቡና አልሚዎችና ላኪዎች ማህበር ፕሬዝዳንት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በአስተላለፉበት ወቅት ይህ የስልጠና መድረክ በተለይም ለቡና መሠረት ለሆነው አልሚዎችና ኤክስፖርተሮች ያለው ፋይዳ እጅግ የላቀ ነው ብለዋል፡፡

ስልጠናውን በይፋ የከፈቱት የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ ናቸው፡፡ ዶ/ር አዱኛ በመክፈቻ ንግግራቸው ወቅት በቡና ዘርፍ የተሻለ በመስራት ቡናን ለዓለም እና ለሀገር ውስጥ ገበያ በጥራት ለማቅረብ በዋናነት ወደታች ወርዶ አርሶ አደሩን እና የአልሚውን ማህበር አባላት ብቁ ማድረግ፣ማሳመንና ማሰራት ስለሚገባ ስልጠናውን እና ልምዶችን በትኩረት ተከታለን ልንሰራበት ይገባል ብለዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ቡና ላይ ውጤት ማምጣት የሚቻለው በዕውቀትና በምርምር መደገፍ ሲቻል በመሆኑ በቅንጅት ልንሰራበት ይገባናልና በአላችሁ አቅምና ሙያ ለዩንቨርስቲዎች፣ለምርምር ማዕከላትና በዘርፉ ለሚሰሩ ተቋሞቻችን ድጋፍ እንድታደርጉ እንጠይቃለን በማለት መልካም የስልጠና ጊዜ እንዲሆን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቡና አልሚዎችና ላኪዎች ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሁሴን አምቦ በበኩላቸው ቡና 5.2 ሚሊዮን የሚሆን ቡና አምራች ገበሬዎችን፣ከ30 ሚሊዮን በላይ የሀገሪቱ ዜጎች የሚተዳደሩበት እና ከ30 እስከ 40 ሚሊዮን የሚደርሰውን የውጪ ምንዛሪ የሚያመነጭ ነው ብለዋል፡፡ዶ/ር ሁሴን በመሆኑም እኛ አምራች አርሶ አደሮች እጅግ ደስ ሊለን ይገባል ሲሉ ገልፀዋል፡፡ ዶ/ር ሁሴን አክለውም ከቡና ምርት፣ዝግጅት እስከ መላክ ድረስ የቡና ዱካን ማስጠበቅና ለጥራት መስራት ይመለከተናል ብለዋል፡፡ በመሆኑም በዚህ ረገድ ሰባት የሚሆኑት ማህበራት ሚና በቀላሉ የሚታይ ባለመሆኑ ስለቡና ጥራት የሚሰጠው ስልጠና ተጠናክሮ ሊሰጥ ይገባል ብለዋል፡፡ የገበያ ማፈላለግና የፕሮሞሽን ስራ እጅግ ወሳኝ ነው ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ እንደበፊቱ በባለልዩ ጣዕም ቡና(CoE) ውድድር ላይ አልሚዎች በአቅማቸው ልክ መሣተፍ ያለባቸው በመሆኑ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ጋር በመጣመር ተግባራዊ እንዲደረግ የፊርማ ስነ-ስርዓት የተፈፀመ ስለመሆኑና የቡና አ/አደሮች እንዲሳተፉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ዶ/ር ሁሴን የአውሮፓ ህብረት የፀረ-ደን መመሪያ(EUDR) በተመለከተ የድርጊት መርሃ-ግብር ዕቅድ የተዘጋጀ ሲሆን ዕቅዱን ለመተግበርም የማህበራችንና አባላቱ ሚና በተለይም ለእኛ አልሚዎች ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ስለሆነ በኃላፊነት ልንሰራበት፣በትኩረት ልንሳተፍበት ይገባል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቡና አልሚዎችና ላኪዎች ማህበር(ECGPEA) ሲኒዬር የግብርናው ዘርፍ አታቼና በአሜሪካ የውጪ ግብርና ዘርፍ ከፍተኛ አስተባባሪ የሆኑት ሚስ ጀስቲኒያ ቶሪ በበኩላቸው በኢትዮጵያ በአለው የቡና ዓይነትና የቡና አመጣጥ ታሪክ በጣም የሚደመምቡትና ሀገሪቱ በቡና ግብይት ረገድ ያለችበት ደረጃ በድጋሚ የሚያስደንቀኝ ነው ብለዋል፡፡ሚስ ጀስቲንያ የኢትዮጵያ ቡና በሁሉም ዓለማት በተለይም በጀርመን፣አሜሪካ፣ሳዑድ አረቢያ እና በሌሎች ዓለም አቀፍ ሀገራት ተወዳጅ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ አክለውም በአሜሪካ 400 ሚሊዮን ስኒ ቡና በቀን እንደሚጠጣ በአጠቃላይ ከ100000 ቢሊዮን ስኒ ቡና በዓመት እንደሚጠቀሙና ይህም ሆኖ በዓለም በ25ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡ ሚስ ጀስቲንያ አያይዘውም በዓለም ቡና ተጠቃሚ ከሆኑት ሀገራት ፊንላንድ በቀዳሚው ደረጃ እንደምትገኝና ስራ እንዲሰራበት የቤት ስራቸውን ሰጥተዋል፡፡

ሚስ ጀስቲንያ ምንም እንኳን በቡና ታሪክ ኢትዮጵያ ቀዳሚ ብትሆንም የሀገሪቱ የቡና ግብይት ሰንሰለት ግን ተጠቃሚነታችን አንፃር እንደጠበቅነው አይደለም ብለዋል፡፡ በመሆኑም ከቴክኖሰርቭ እና ዩ.ኤስ.ዲ.ኤ ጋር ከ2021 እ.ኤ.አ ጀምሮ በመቀናጀት በተወሰኑ ፕሮግራሞች በተለይም ይርጋጨፌ ላይ ስራዎችን እየሰራን ነው ሲሉ አክለው ገልፀዋል፡፡ ስራቸው በተለይም በስፔሻሊቲ ቡና ላይ ትኩረት በማድረግ እንደሚሰሩና የዛሬውም ወርክሾፕ እኒህንና ሌሎች በርካታ ጉዳዮች ትኩረት ያደርጋል ብለው እንደሚጠብቁ እምነታቸውን ገልፀዋል፡፡ አክለውም ከዚህ ስልጠና ያላቸውን ግምት ምርት በመጨመርና ጥራት በመጠበቅ፣ኤክስፖርት ገቢን ከፍ በማድረግ ኢኮኖሚያዊውን ጠቀሜታ ወደላቀ ደረጃ ማድረስ እንደሚሆን ተስፋ አለኝ ብለዋል፡፡ ሚስ ጀስቲንያ የአካባቢ የአየር ፀባይ ጋር በተያያዘ ዋነኛው ተግዳሮት መሆኑ. ማህበራዊና አካባቢያዊ ሁኔታን ማጣጣም፣ የምርት ዘር እጥረት ችግር መኖሩ እና የደንበኞች ፍላጎት መቀያየርና ሌሎች ተግዳሮቶች እንዳለባችሁ ቢታወቅም ይህን ሁሉ ችግር ለመቅረፍ የአንድ ቀን ስልጠና ይፈታል ብለው እንደማያምኑ አስረድተዋል፡፡ ነገርግን ይላሉ ሚስ ጀስቲና የእናንተ ጥረት ተጨምሮ ተግዳሮቶች ሊፈቱ እንደሚችሉ እምነቴ ነው ብለዋል፡፡ በስተመጨረሻም እነዚህን ሁሉ ተግዳሮቶች ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን፣ ከቴክኖሰርቭ፣ ዩ ኤስ ኤ ዲ እና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን ችግሮችን መወጣት እንደሚገባ ገልፀው አሜሪካ በ2021 ከ9 ቢሊዮን ዶላር የዓለም ቡና ገበያን ድርሻ የያዘች ሲሆን 2 በመቶው ከኢትዮጵያ የመጣው ቡና ላይ በመሆኑ አቅሙን መጠቀም ይገባል ሲሉ ጥቆማቸውን የሰጡ መሆኑን የባለስልጣን መ/ቤቱ የህዝብ ግንኙነትና የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቡድን በቦታው ተገኝቶ ዘግቧል፡፡

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *