1

የቡና ኮንፍረንስና ኤግዚቢሽን ሊካሄድ ነው

****************

ጥር 22/2016 ዓ.ም

ክቡር የቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) በዛሬው እለት የተለያዩ የመንግስት እና የግል ሚዲያዎች በተገኙበት በመጪው ሳምንት አለማቀፍ የቡና ኮንፍረንስና ኤግዚቢሽን መካሄዱን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ክቡር ዋና ዳይሬክተሩ እንደገለፁት፤ ከ800 በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ድርጅቶች የሚሳተፉበት የመጀመሪያው “የአፍሪካ የቡና ሳምንት በኢትዮጵያ” እና 20ኛው የአፍሪካ ኮፊ አሶሴሽን ኮንፍረንስና ኤግዚቢሽን ከጥር 28 እስከ የካቲት 2 /2016 ዓ.ም. በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ ተናግረዋል፡፡

ለአንድ ሳምንት በሚቆየው ኮንፍረንስና ኤግዚቢሽን ላይ የተለያዩ ታዋቂ ሰዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ አለማቀፍ ቡና ገዢዎች እንዲሁም መንግስታዊ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የተለያዩ አገራት ኤምባሲ ተወካዮች ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡ የ25 ቡና ላኪ አፍሪካ ሀገራትና የቡና ገዢ ሀገራት የግብርና ሚኒስትሮች መጋበዛቸውን አስረድተዋል።

በኮንፍረንስና ኤግዚብሽኑ ድርጅቶች ምርታቸውን እንደሚያስተዋውቁ፤ ዝርዝር ጥናቶች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው እና በጅማና ሃዋሳ የጉብኝት መርሃ ግብር እንደሚኖር ክቡር ዶ/ር አዱኛ ደበላ ገልጸዋል።

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *