335623013_1250278139238710_5149716227197245019_n

‹‹የየድርሻችንን መወጣት አለብን፤ በዓመት አንዴ ብቻ ማክበር መሆን የለበትም፡፡››

የኢትዮጵያ ቡና ሻይ ባለስልጣን በዘንድሮ ዓመት ‹‹እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ›› በሚል የሀገር አቀፍ መሪ ቃልና ‘’Innovation and Technology for Gender Equality” በሚል ኣለማቀፍ መሪ ቃል የሴቶች እኩልነት ቀንን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች አከበረ፡፡ በዝግጅቱን መክፈቻ መርሀ ግብርሩ ላይ አቶ መሐመድ ሸምሱ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈጻሚ እና አቶ ሰፊሳ አባቡ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ በዓሉን አስመልክቶ መልእክቶችን ያስተላለፉ ሲሆን የስራ አመራር ስራ አስፈጻሚው እንዳሉት ‹‹በዓሉን ዓመት እየጠበቁ ማክበር ብቻ ሳይሆን ለጾታ እኩልነት በየጊዜው ሁሉም የየድርሻውን መወጣት እንዳለበትና በስርአት ሁሉም ተገኝቶ ማክበር እንዳለበት›› አሳስበዋል፡፡ የጾታ እኩልነትን ከማስፈን አንጻር ‹‹ወደታች እንዴት ማውረድ እንደሚገባም›› አስገንዝበዋል፡፡ በዋናነት ደግሞ ‹‹ከተቋማችን ጋር ማስተሳሰሩ ላይ አጠናክሮ መሄድ እንደሚገባ›› አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

ጽ/ቤት ሃላፊው አቶ ሠፊሳ አባቡ በበኩላቸው ‹‹በዓሉ በቀላሉ እንዳልመጣ፤ ስለሆነም ከልባችን ማክበር እንዳለብን፤ ከዳር (በገጠሪቱ) ያሉት ይበልጥ ተጎጂ እንደመሆናቸው ማገዝ እንደሚገባ›› ተናግረዋል፡፡ በማስከተልም ዝግጅቱን ስፖንሰር ያደረጉትን Spanish Cooperation እና DeSIRA PARTNERSHIPS FOR INNOVATION እንዲሆንም መድረኩን ያዘጋጁትንና የመሩትን የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አካላትን አመስግነዋል፡፡

በማስከተልም አቶ አያሌው አቸነፍ የሴቶች ሕጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ባለሞያ አጠቃላይ የሴቶች እኩልነት አስመልክቶ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በሀገራችን ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ በአመራርነትም ሆነ በሌሎች ትልልቅ ዘርፎች ሚና የተጫወቱ ሴቶችን ያነሱ ሲሆን የዘንድሮው የሴቶች ቀን አስተዋጽኦ የበረከቱ ሰዎችን የሚታሰብበት፣ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋዎች የተጎዱ ሴቶች ትኩረት የሚሰጥበት፣ ሠላምን ከማስፈን አንጻር ሚና ስለመጫወት፣ ሴቶች በኢኮኖሚም የተሻለ ሕይወት የሚመሩበት፣ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች የሚቀንሱበት ስራ የመስራት ዓላማዎችን ያነገበ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ ሰነዱ ከቀረበም በኋላ አጠቃላይ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

በዝግጅቱ ወቅት YB interteainment ልዩ ልዩ የኪነጥበብ ዝግጅቶችና የጥያቄና መልስ ውድድር በማካሄድ የሴቶች እኩልነት ላይ ግንዛቤን የሚያስጨብጡ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡ በተጨማሪም የወረዳ 07 ሴቶች ማኅበር ላበረከተው የሴቶች እኩልነት ማስፈን ስራ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የስጦታ ማበርከት ስነስርዓት ፈጽሟል፡፡

የሕዝብ ግኑኝነትና ተግባቦት ባለሞያ በቦታው ተገኝቶ ዘግቦታል

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *