13

የጅማ ምርት ጥራት ምርመራ እና ሰርቲፊኬሽን ማዕከል በይፋ ተመረቀ!!

መጋቢት 28/2015

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በጅማ ከተማ ያስገነባው የምርት ጥራት ምርመራ እና ሰርቲፊኬሽን ማዕከል በዛሬው እለት ከፍተኛ የፌዴራል እና የክልል ባለስልጣናት እንዲሁም የዞን እና ወረዳ አመራሮች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ በይፋ ተመርቋል:: የሀገር ሽማግሌዎች: የሀይማኖት አባቶች: የተለያዩ ማህበራት: ዩኒቨርሲቲዎች: በዘርፉ ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችም ተሳትፈዋል::

የተከበሩ አቶ ሰለሞን ላሌ በኢፌዲሪ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ እንዳሉት በባለስልጣን መ/ቤቱ እና በክልሉ የተቀናጀ ስራ የማዕከሉ እውን መሆን እንዳስደሰታቸው እና ከዚሁ ጋር ተያይዞ በርካታ እድሎችን ይዞ እንደሚመጣ ገልፀ ዋል:: አያይዘውም በተለይ በዘርፉ ላይ የተሰማሩ አ/ አደሮች: አቅራቢ እና አልሚዎችም ይደርስባቸውየነበረውን እንግልት ለመቀነስ: አ.አበባ ድረስ ምርታቸውን ለማጓጓዝ ለነዳጅ እና መኪና ኪራይ ያወጡ የነበረውን ወጪ ለማስቀረት እንዲሁም ቡናቸውን እስከሚያስመረምሩ ድረስ ይባክን የነበረ ጊዜ ሙሉ በሙሉ እንደሚያስቀር ተናግረዋል::

ክብርት የግብርና ሚ/ር ዴኤታ ዶ/ር ሶፊያ ካሳም ለአገራችን የውጪ ምንዛሪ ግኝት ከፍተኛ አስተዋፅዖ በማበርከት ላይ የሚገኘው ቡና በተለያየ ደረጃ የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሀገሪቱ ዜጎች መተዳደሪያ እንደሆነ እና መንግስትም በዘርፉ የሚገኙትን አ/ አደሮች ችግር ለመፍታት በስፋት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ አስረድተው; ይህ በዛሬው እለት የተመረቀ ማዕከል ይታዩ የነበሩ አንዳንድ ችግሮች በተለይም በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የነበሩ ክፍተቶችን ለመሙላት : ወደ ታች ለማውረድ እና በምርቱ ጥራት ላይ ይታዩ የነበሩ የጥራት ችግሮች ለመቅረፍ እንደሚያግዝ ገልፀዋል::

ክቡር ዶ/ር አዱኛ በበኩላቸው ተገቢውን ጥናት በማድረግ አ/አደሩን: አልሚውን:አቅራቢውን እና ባለ ሀብቱን ጭምር ጊዜውን:ገንዘቡን እና ውጣ ውረዱን መቀነስ የሚያስችሉ አሰራሮችን መቀየስ እንደሚገባ ታምኖበት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል:: የምርት ጥራት ምርመራ እና ሰርቲፊኬሽን አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ እና የማዘመን ስራውንም ጎን ለጎን የማስኬዱ ስራ ቢሰራ ትልቅ ለውጥ እንደሚመጣ በማሰብ ወደ ተግባር መገባቱንም ጠቁመዋል::

ቀደም ሲል በአ/አበባ እና ድሬዳዋ ከተሞች ብቻ ተወስኖ የቆየውን የምርት ጥራት ምርመራ የስራ እንቅስቃሴ በጅማ እና ሀዋሳ ከተሞችም እንዲሰፋ ለማድረግ በስትራቴጂ በተቀመጠው መሠረት 8 ማዕከላት በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ቨመገንባት አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ መታቀዱን ገልፀው ዛሬ የተመረቀው ማዕከልም የዚሁ አካል እንደሆነ ጠቁመዋል::

በዚህ ማዕከል የሚሰጠው ከቀጥታ ግብይት ትስስር ጋር የተያያዘ ስራ ሲጀመርም ከሚዛን አገልግሎት: ከክፍያ መዘግየት: ከገንዘብ እጥረት እና የመሳሰሉ ጉዳዮች ጋር ይነሱ የነበሩ ቅሬታዎችን እንደሚያስቀር የተናገሩ ሲሆን የከተማዪቱን ገቢ ለማሳደግ: በአካባቢው የተነቃቃ የንግድ እንቅስቃሴ እንዲኖር እና ለወጣቱ ከፍተኛ የስራ ዕድል ለመፍጠር እንደሚያግዝ አስረድተዋል::

ክቡር ዋና ዳ/ር በመጨረሻ ንግግራቸው ተቋሙ ለዚህ እንዲበቃ ያገዙ አካላትን ሁሉ አመስግነዋል:: ከዚህ በመቀጠል ከፍተኛ አመራሮቹ ማዕከሉን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን የላቀ አስተዋፅዖ ላበረከቱ ማበረታቻ ሽልማት ተሰጥቷል::

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *