306967930_396393952664893_668980806608691014_n

‘’የኢትዮጵያ ቡና እሴት ተጨምሮበት ወደውጭ ቢላክ የጋራ ተጠቃሚነት ይጎለብታል፡፡’’ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ

መስከረም 11 ቀን 2015 ዓ.ም የኢትዮጵያን ቡና ለቻይና ገበያ የሚያቀርበው ለቡና የተባለ ኩባንያ ሺያዎካሺያ ከተባለ የቻይና ዲጂታል ማስተዋወቂያ ኩባንያ ጋር በትብብር ለመስራት ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት ክቡር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ባደረጉት ንግግር ሁለቱ ኩባንያዎች የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው የኢትዮጵያን ቡና ለቻይናውያን ተጠቃሚዎች በስፋት በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ያሉ ሲሆን ቡናው ከመገኛው እሴት ተጨምሮበት ወደ ቻይና ቢገባ ደግሞ የጋራ ተጠቃሚነት ይጎለብታል ብለዋል፡፡

ቻይና የኢ-ኮሜርስ ግብይት ቴክኖሎጂን በመጠቀም ከ50% በላይ የሆነውን የአገሪቱ ሽያጭና ግዥ ታሳልጣለች ያሉት አምባሳደር ተሾመ ቴክኖሎጂው በአጠረ ጊዜ ውስጥ የግብይት መረጃውን በአንድ ጊዜ ለበርካታ ተጠቃሚ ማዳረስ የሚያስችል በመሆኑ ገበያን በማሳለጥ ረገድ እጅግ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያም የኢ-ኮሜርስ ግብይትን በመጠቀም ምርቶቿን ለአለም ገበያ እያቀረበች መሆኗንም ገልጸዋል፡፡

አምባሳደር ተሾመ በንግግራቸው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አሊባባ የግብይት መረብን በመጠቀም የኢትዮጵያ ምርቶች ለገበያ መቅረባቸውን ጠቁመው ከቡና ውጭ ያሉትንም እንደ ሰሊጥ፣ ማሾና አኩሪ አተር የመሳሰሉ ምርቶችን በዚሁ የመገበያያ ዘዴ ውስጥ እንዲካተቱ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቡና የሚመረተው ከድካማችን ተጠቃሚ እሆናለን በማለት በትጋት ከሚሰሩት አርሶአደሮች ነው ያሉት አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ከቡና አስመጭና ላኪ ኩባንያዎች የሚጠበቀው እነዚያ ታታሪ የቡና አምራች አርሶ አደሮች የድካማቸውን ያክል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ነው፡፡

አምባሳደር ተሾመ አክለውም ሁሉምንም ወገን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፍትሃዊ ንግድ እንዲኖር ለማስቻል በግብርና ምርቶቻችን ላይ እሴት መጨመር ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም እንደ ‘ለቡና’ ያሉ የኢትዮጵያ ቡና አስመጭና ላኪ ኩባንያዎች በምርቱ ላይ እሴት በመጨመር ረገድ በጋራ ልንረባረብ ይገባል ያሉት አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ኩባንያዎቹ ምንጊዜም ቢሆን የኢትዮጵያን ቡና ትክክለኛነት እና ልዩ ባህሪ አረጋግጠውና እውቅና ሰጥተው እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በፕሮግራሙ 52 ሰዎች ተሳትፎ ያደረጉበት የቡና ቅምሻ ስነስርዓት ተካሂዷል፡፡

September 21/2022, LeBuna, the company which supplies Ethiopian coffee to the Chinese market signed an agreement to work together with XiaoKaXia, the Chinese digital promotion company.

During the signing ceremony Ambassador Teshome Toga, who made an opening remark, stated that reaching the agreement between the two companies will have its own great contribution to enhance the promotion of Ethiopian Coffee.

He noted that China has played very important role using e-commerce technology and almost more than 50% of the transaction activities are run through different e-commerce platforms.

In his speech, Ambassador Teshome pointed out that Ethiopian products have recently been marketed using Alibaba’s e-commerce platform, and needs to exert more effort to produce and bring to the market various coffee types and other agricultural products like sesame, mung bean, soybean and so on.

Furthermore, the Ambassador underscored that coffee in Ethiopia is produced by smallholder farmers who toll and sweat to benefit from their hard work and he stressed that Ethiopia needs fair trade that benefits all and this can best be done if the companies could add value to Ethiopian products.

Finally he called up on the enterprises, like Lebuna and others to work for adding value to Ethiopian coffee and to always certify and acknowledge the originality and specialty of the Ethiopian coffee.

In the program a coffee tasting ceremony has conducted, in which 52 individuals were participating.

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *